‎የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ እና እየተገነቡ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

You are currently viewing ‎የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በአዲስ አበባ የተገነቡ እና እየተገነቡ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

AMN ግንቦት 14/2017

ባለሙያዎቹ በቦሌ ክፍለ ከተማ ተጀምረው በአጭር ጊዜ የተጠናቀቁና እየተጠናቀቁ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

‎በክፍለ ከተማው በመጀመሪያው ዙር የለሙ የኮሪደር ቦታዎች፣ በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት እየለሙ ያሉ ልማቶች፣ የቦሌ ቡልቡላ ፓርክ፣ በወረዳ 7 በአጭር ጊዜ ተጀምሮ ወደመጠናቀቅ ምዕራፍ የደረሰ ደረጃውን የጠበቀ ጤና ጣቢያ፣ የወጣት ሰብዕና መገቢያ፣ የማስፋፊያ የተደረገባቸው የትምህርት ተቋማትና ሌሎችም የጉብኝቱ አካል ናቸው።

‎በጉብኝት የክፍለ ከተማው የስራ ሀላፊዎች፣ የሚዲና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችን ጨምሮ ታዋቂ አርቲስቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

‎ከጉብኝቱ በኋላ ውይይት እንደሚካሄድ ተመላክቷል።

በሄለን ጀምበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review