
AMN-ኅዳር 19/2017 ዓ.ም
የማህበረሰብ አንቂዎች እና የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎች የዲጂታል ሚዲያን በመጠቀም ኢትዮጵያን ሊያጎሉ እና አንድነቷን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ሃሳቦችን ሊያንፀባርቁ ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢሮ ኃላፊ ሚኤሳ ኤሌማ (ዶ/ር) ተናገሩ።
“ዘመኑን የዋጀ የተግባቦት ስራ ለሀገር ልዕልና” በሚል መሪ ሀሳብ ለህዝብ ግንኙነት አመራሮች እና ማህበረሰብ አንቂዎች ስልጠና ተሰጥቷል።
የከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢሮ ኃላፊ ሚኤሳ ኤሌማ (ዶ/ር) የማህበረሰብ አንቂዎች እና የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎች የዲጂታል ሚዲያ በመጠቀም ኢቲዮጵያን ሊያጎሉ እና አንድነቷን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ሃሳቦችን ሊያንፀባርቁ ይገባል ብለዋል።
በከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት፣ በአዲስ አበባ ባህል ፣ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ እና በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሚዲያ ዘርፍ በጋራ በተዘጋጀው ስልጠና ላይ ተገኝተው ንግግር ያረጉት በአዲስ አበባ ባህል ፣ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ካላት የቱሪዝም ሃብት ተጠቃሚ እንድትሆን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያዎች እና የማህበረሰብ አንቂዎች ዲጂታል ሚዲያውን በመጠቀም የመስዕብ ሀብቶችን ማስተዋወቅ እንዳለባቸው ገልፀዋል።
በአሸናፊ በላይ