የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ምርትን በመተካት አበረታች ውጤት እያመጣ ነው

You are currently viewing የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ምርትን በመተካት አበረታች ውጤት እያመጣ ነው

AMN- ህዳር 11/2017 ዓ.ም

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የወጭ ንግድን በማሳደግና ገቢ ምርትን በመተካት አበረታች ውጤት እያመጣ መሆኑን የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ገለፀ።

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀድጎ ኃይለኪሮስ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ መንግሥት ለአምራች ዘርፉ የሰጠው ልዩ ትኩረት ለኢንዱስትሪ ዘርፉ እድገት አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢንዱስትሪዎች በመገኘት በሚሰጡት አቅጣጫ የኢንዱስትሪዎች ችግር እየተፈታ መሆኑንም ተናግረዋል።

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በ2017 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የወጭ ንግድ አፈፃፀም እድገት እንዲያሳይ ማስቻሉን ገልፀዋል።

በሪፎርሙ የውጭ ምንዛሬ ተመን ማስተካከያ መደረጉ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባውን የወርቅ ክምችት ማሳደጉን ጠቅሰዋል።

እንዲሁም የቡና ወጪ ንግድ ከመቼውም ጊዜ በላቀ ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን ገልጸው፤ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የወጭ ንግድ አፈፃፀም ከእቅዱ በላይ አመርቂ ውጤት ማስመዘግቡን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና የኢንዱስትሪዎችን ችግር መፍታት መቻሉንም ተናግረዋል።

አሁን ላይ ኅብረተሰቡ የአገር ውስጥ ምርትን በስፋት መጠቀም በመጀመሩ ገቢ ምርትን ለመተካት እድል መፍጠሩን ነው ያስረዱት።

የተኪ ምርቶች ስትራቴጂ መተግበሩ በርካታ ምርቶችን በአገር ውስጥ በማምረት ለማኅበረሰቡ ለማቅረብ ማስቻሉን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review