የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው እንዲጨምር አስችሏል – አቶ መላኩ አለበል

You are currently viewing የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው እንዲጨምር አስችሏል – አቶ መላኩ አለበል

AMN- የካቲት 28/2017 ዓ.ም

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አምራች እንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው እንዲጨምር ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።

አቶ መላኩ አለበል በአዲስ አበባ የተገነባውን የክሮታጅ ጣህኒያ ሰሊጥ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ጎብኝተዋል።

ድርጅቱ እሴት የተጨመረበትን የሰሊጥ ምርት በማምረት ሙሉ በሙሉ ወደ ውጭ የሚልክ መሆኑ ተገልጿል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፣ ፋብሪካው ደረጃውን በጠበቀ እና ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ባሟላ መንገድ እሴት የተጨመረበት የሰሊጥ ምርት እያቀረበ መሆኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው እንዲጨምር ማስቻሉን ተናግረዋል።

በዚህም በዘርፉ የሚገኘው የገቢ መጠን ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸዋል።

እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ለገበያ ማቅረብ ገቢን ለማሳደግ እንዲሁም በእሴት ሰንሰለት ውስጥ ያሉ ተዋንያንን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ለአምራች ዘርፉ በርካታ ምቹ ሁኔታዎች እንዳሏትም ጠቁመዋል።

ዘርፉን ለማስፋት እና ለማጠናከር እንዲሁም ማነቆዎችን ለመፍታት በሀገር አቀፍ ደረጃ ካውንስል መቋቋሙን ገልጸው፣ በዚህም ውጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የክሮታጅ ጣህኒያ ሰሊጥ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አግአዚ ልዑል በበኩላቸው፣ የተቀነባበሩ የሰሊጥ ምርቶቹ መዳረሻም አሜሪካ፣ አውሮፓ እና መካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች እንደሆኑ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

መንግስት በተለያየ መንገድ ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ገልጸው፣ ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።

የክሮታጅ ጣህኒያ ሰሊጥ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በኢትዮጵያውያን እና አሜሪካውያን ባለሀብቶች የተቋቋመ ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review