የሞጆ ወደብ የሎጂስቲክስ ማዕከል የማስፋፊያ ግንባታ በጥቂት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ማዕከሉ የሎጅስቲክስ አገልግሎት አሰጣጥ እና ቅልጥፍና የመጨመር አቅም እንዳለውም ገልጿል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ አመራሮችና ሰራተኞች የሞጆ ወደብ የሎጂስቲክስ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥና የማስፋፊያ ግንባታ አፈፃፀምን ጎብኝተዋል።
በ2001 ዓ.ም በ1 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ ላይ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን አሁን በግንባታ ላይ ያለውን የማስፋፊያ ግንባታ ጨምሮ 133 ሄክታር ስፋት እንዳለው ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የማስፋፊያው ግንባታ ሂደት ከጥቂት ወራት በኋላ ሲጠናቀቅ የሎጂስቲክስ ዘርፍ የአገልግሎት አሰጣጥ አቅምን በከፍተኛ ደረጃ ከማሳደጉም ባሻገር ቅልጥፍናንም እንደሚጨምር ገልጿል።
ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ማዕከሉ ከባቡር መሥመር ጋር እንዲገናኝ ተደርጎ በመገንባት ላይ እንደሚገኝ እና የቀዝቃዛ ሎጂስቲክስ መጋዘን ጨምሮ ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማቶችን በውስጡ እንደያዘ በመረጃው ተመላክቷል።