የሩስያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል በማዳበሪያ፣ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ በማምረቻ እና በብረታብረት ኢንዱስትሪ ዘርፎች እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል::
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ፣ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ተርኪሂን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው፣ ሩስያ የኢትዮጵያ የሁልጊዜ አጋር ሀገር መሆኗን ገልፀው፣ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት በኢኮኖሚ፣ ዲፕሎማሲ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
የሩስያ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተፈጠረው ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል በማዳበሪያ፣ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ በማምረቻ እና በብረታብረት ኢንዱስትሪ ዘርፎች እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል::
አምባሳደር ኤቭጌኒ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ እና ሩስያ ረዥም ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን አውስተው፣ ግንኙነቱን በኢኮኖሚና በማኀበራዊ ዘርፎች ለማጠናከር ሀገራቸው ዝግጁ መሆኗን ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።