የርዕደ መሬት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዝግጁነታችንና የምላሽ ሁኔታችን ባለን ቴክኖሎጂ፣ ሳይንሳዊ ምርምር፣ ትንተናና የትንበያ አቅም የሚወሰን ነው፡-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የርዕደ መሬት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዝግጁነታችንና የምላሽ ሁኔታችን ባለን ቴክኖሎጂ፣ ሳይንሳዊ ምርምር፣ ትንተናና የትንበያ አቅም የሚወሰን ነው፡-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – ጥር 8/2017 ዓ.ም

የርዕደ መሬት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ዝግጁነታችንና የምላሽ ሁኔታችን ባለን ቴክኖሎጂ፣ ሳይንሳዊ ምርምር፣ ትንተናና የትንበያ አቅም የሚወሰን ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

አቶ ተመስገን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ የስፔስ ሳይንስ እና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ባደረግነው ጉብኝት በርዕደ መሬት ነክ ሳይንሳዊ ምርምር አበረታች ስራዎችን አይተናል ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት ባካሄድነው የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ በርዕደ መሬት ክስተት ዙሪያ ባስቀመጥነው አቅጣጫ መሰረት ወደ ተጠናከረ ተግባር ተገብቷል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አደጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የመሠረተ-ልማት፣ የጊዜያዊ መጠለያ፣ የሰብአዊ ድጋፍ፣ የሳይንሳዊ ትንተና እና ትንበያ ቡድኖችን በማደራጀት በዕቅድ ላይ የተመሰረተ ሥራ እየተከናወነ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

መንግሥት የአጭርና የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ዝግጁነትን ለማጎልበት የጥናትና ምርምር ተቋማት ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂና ብቁ የሰው ኃይል ጠንካራ ቁመና እንዲፈጥሩ ድጋፍ ያደርጋልም ብለዋል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review