የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ…

You are currently viewing የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ…

AMN-ሚያዝያ 13/2017 ዓ.ም

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ የተወለዱት እ.አ.አ ታኅሣሥ 17 ቀን 1936 በአርጀንቲና ዋና ከተማ ቦነስ አይረስ ነው።

ፓፕ ፍራንሲስ ወደ መንበረ ጵጵስና ከመምጣታቸው በፊት ጆርጅ ማሪዮ ቤርጎሊዮ በሚል የዓለም ስም ይጠሩ ነበር።

ፓፕ ፍራንሲስ ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከመመረጣቸው በፊት የአርጀንቲና የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ካርዲናል ሆነው አገልግለዋል።

ፖፕ ፍራንሲስ እ.አ.አ. ከ2005 እስከ 2011 የአርጀንቲና ጳጳሳት ኮንፈረንስ ፕሬዝዳንትም ነበሩ።

ሊቀ ጳጳሱ እ.አ.አ መጋቢት 13 ቀን 2013 ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛን በመተካት ነበር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት።

ፖፕ ፍራንሲ እ.አ.አ በ2013 በታይም መጽሔት የዓመቱ ምርጥ ሰው ተብለውም ተመርጠው ነበር።

ሊቀ ጳጳሱ ባለፉት ወራት የሳንባ ምች (ኒሞኒያ) የጤና እክል ገጥሟቸው በህክምና ርዳታ ላይ ነበሩ።

ፖፕ ፍራንሲስ በዛሬው ዕለት በ88 ዓመት ዕድሜያቸው ማረፋቸውን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማስታወቋን ተከትሎ በመላው ዓለም የሚገኙ የእምነት ተከታዮች እና የአገራት መሪዎች ሐዘናቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

በትሁት ባህሪያቸው የሚታወቁት ሊቀ ጳጳሱ ለተጎዱ እና ለአቅመ ደካሞች ድምፅ በመሆን ባህሪያቸው ይታወቃሉ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review