• የግል ድርጅቶች የአክስዮን ድርሻ በመሸጥ የድርጅታቸውን ካፒታል ለማሳደግ እና ለማስፋፊያ ይጠቀሙበታል
• የመገበያያ መድረኩ ምርት፣ አገልግሎት እና ሐሳብ የሚሸጥበት በመሆኑ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ሐሳባቸውን እንዲሸጡ ዕድል ይፈጥርላቸዋል
• ማንኛውም ድርጅት ለሽያጭ ከመቅረቡ በፊት ተፈትሾ ጥቅም እና ጉዳቱ ተጠንቶ ለገበያ የሚቀርብ በመሆኑ አስተማማኝ ነው
• የውጭ ኢንቨስተሮች የኩባንያ ድርሻ እንዲገዙ ዕድል የፈጠረ በመሆኑ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ያግዛል
• የመንግሥትን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው
የምጣኔ ሃብት ምሁሩ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ በሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ዙሪያ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ