
AMN – ታኀሣሥ 3/2017 ዓ.ም
የሲቪል ምዝገባ ስርዓት በተሻለ ቴክኖሎጂ መሰረት ላይ እንዲገነባ አዲስ አበባ የወሰደችው ቆራጥ እርምጃ የሚደነቅ መሆኑን የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ፡፡
በፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የተመራና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላን ያካተተው የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን በሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና መስርያ ቤት በመገኘት የሪፎርም ስራ አፈፃፀም ጉብኝት አድርጓል።
በዕለቱ ኤጀንሲው እያከወነ ያለውን የተቋም ግንባታ ስራ ያለበትን ደረጃ ለሱፐርቪዥን ቡድኑ በኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ በተቋም ግንባታው የከተማዋን የዲጂታል አገልግሎት የላቀ በማድረግ ስማርት ሲቲን ለመገንባት እየተሰሩ ያሉ የቴክኖሎጂ ማሻሻያ ስራዎችን እንዲሁም የሲቪል ምዝገባ ስርዓት ላይ ከጤና እና ፍርድ ቤቶች ጋር ያለውን ቅንጅት ገለጻ አድርገዋል፡፡
እንዲሁም የየዲጂታል አገልግሎት መቆራረጥን በአዲስ ስርዓት ተክቶ በመፍታት የተገልጋይ እርካታን ለማሻሻል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተጨማሪነትም በከተማው ያለውን የፋይዳ ምዝገባ አሁናዊ ሁኔታም አቅርበዋል።
ዶ/ር ፍፁም በተቋሙ የመጣው ለውጥ ለሌሎች ተቋማት ልምድ የሚሆን መሆኑን ገልፀው የሲቪል ምዝገባ ስርዓት በተሻለ ቴክኖሎጂ መሰረት ላይ እንዲገነባ አዲስ አበባ የወሰደችውን ቆራጥ እርምጃ አድንቀዋል፡፡
የዘርፉ መጠናከር ለሃገሪቱ የልማት እቅድ የሚኖሩው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል።
ሚኒስትሯ ተቋሙ ያሳየው ለውጥ ተገልጋይ ጋር ሊመነዘር የሚችል የአገልግሎት እርካታ ማምጣት እንዲችል የተጀመሩ የቴክኖሎጂ ስራዎች በፍጥነት እንዲጠናቀቁና የተሟላ ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ላይ የተሰራውን ስራ አበረታች መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ያነሱ ሲሆን ሪፎርሙ የተመራበትን መንገድ እንዲሁም ቴክኖሌጂን ለመተግበር በከተማው የተወሰደው ቁርጠኝነት የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል።
አምስት ሚልዮን ኮደርስን ለማፍራት በተጀመረው ፕሮግራም በቅርቡ ኤጀንሲው የወሰደውን ቁርጠኝነት ተምሳሌት አድርጓ መስርያ ቤታቸው የወሰደ መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር በለጠ በዘርፉ አስፈላጊውን ድጋፍ ሚኒስትር መስርያ ቤታቸው የሚያደርግ መሆኑን ቃል ገብተዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ በበኩላቸው፣ በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለቡድኑ ማስጎብኘታቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡





All reactions:
4141