
AMN- ህዳር 9/2017 ዓ.ም
የስንዴ መኸርን የመሰብሰብ ሒደት በመጀመሩ ከአጨዳ እስከ ጎተራ የሁሉም እገዛ ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሳሰቡ።
በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት የስንዴ መከር ተጀምሯል ብለዋል።
እናም በዚህ ዓመት ብዙ ምርት ስላለን ይህን ሂደት በሀገር አቀፍ ደረጃ በትብብር ማፋጠን አለብን ሲሉ ገልጸዋል ።
ከአጨዳ እስከ ጎተራ የሁላችንንም ትግግዝ ይፈልጋል ሲሉም አመልክተዋል ።
በተጨማሪም ለመጪው የበጋ የስንዴ ምርት መዘጋጀት አለብን ብለዋል።