የስፖርት ዘርፉ የህዝቡን አንድነትና አብሮነት የበለጠ ማጠናከር እንዲችል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ

You are currently viewing የስፖርት ዘርፉ የህዝቡን አንድነትና አብሮነት የበለጠ ማጠናከር እንዲችል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ

AMN ሰኔ 09 /2017

6ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ውድድር ለ10 ቀናት በጅማ ከተማ የሚካሄድ ሲሆን ዝግጅቱን አስመልክቶ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህል ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መክዩ መሀመድ፤ ስፖርት ከመዝናኛነት ባለፈ ለማህበራዊ ትስስር ትልቅ ፈይዳ አለው።

በዚሁ መነሻነት ኢትዮጵያ በስፖርት ዘርፉ የህዝቡን አንድነትና አብሮነት የበለጠ ማጠናከር እንዲችል የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

በተለይም ስፖርት ከመዝናኛነት ባለፈ ለማህበራዊ ትስስር ማጠናከሪያ እንዲውል አገራዊ ውድድሮች እየተዘጋጁ መሆኑንም ገልጸዋል።

እነዚህ ውድድሮች የህዝቡን አንድነትና አብሮነት እያጠናከሩ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ ረገድ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል።

በመድረኩ ላይም “ስፖርት ለብሄራዊነትና ለማህበራዊ አብሮነት ያለው ፋይዳ” በሚል መሪ ሀሳብ የውይይቱ መነሻ ጽፍ ያቀረቡት በሚኒስቴሩ ስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ መሀመድ፤ ስፖርት ለኢኮኖሚ መነቃቃት፤ ለማህበራዊ ግንኙነት እና አብሮነት ያለው ፋይዳ ትልቅ ነው ብለዋል።

ስፖርት ጠንካራና ጤናማ ትውልድ እንዲሁም አንድነትን ለመፍጠር የሚያግዝ በመሆኑ ለዘርፉ ሁለንተናዊ እድገት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ማደግ እንዳለበት ማንሳታቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

6ኛው የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታ ውድድር ነገ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የመክፈቻ መርሀግብር የሚካሄድ ሲሆን ለዚህም ሲባል ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎችም እንግዶች ወደ ጅማ ከተማ እየገቡ ነው።

+2

See insights and ads

Boost post

All reactions:

3030

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review