የሸዋል ዒድ በአልን በስኬት ማጠናቀቅ የሚያስችል አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል – የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

You are currently viewing የሸዋል ዒድ በአልን በስኬት ማጠናቀቅ የሚያስችል አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል – የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

AMN- መጋቢት 26/2017 ዓ.ም

የሸዋል ዒድ በአልን በስኬት ማጠናቀቅ የሚያስችል አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን እንደገለጹት በክልሉ ከነገ ጀምሮ የሚከበረው የሸዋል ዒድ በአል በስኬት ማጠናቀቅ የሚያስችል አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በአሉ በስኬት እንዲከበር ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በጋራ በመቀናጀት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወናቸውንም አስታውቀዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም በአሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከሁሉም ወረዳዎች ከተውጣቱ የጸጥታ አካላት ጋር የጋራ ምክክር በማድረግ ወደ ስራ መገባቱንም ተናግረዋል፡፡

በአሉ በሚከበርባቸው ስፍራዎችና አካባቢዎች በቂ የጸጥታ ሃይሎችን በማሰማራት የቅድመ ዝግጅት ስራ መሰራቱን በመግለጽ በአሉ በሰላም ተጀምሮ በስኬት እስከሚጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊው የጸጥታ ስራ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

ሁሉም የክልሉ ነዋሪም በዓሉ በስኬት እንዲከበር የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ነው ያሉት።

በተለይም ወጣቱ ለበዓሉ በስኬት መጠናቀቅ የሚጠበቅበትን ከፍተኛ ሃላፊነት ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም በበዓሉ ዋዜማና በዕለቱ የሚፈጠረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ እንዲቻል የተወሰኑ መንገዶች ለትራፊክ ዝግ እንደሚሆኑ መጠቆማቸውንና በአሉ የሰላም፤ የአንድነትና የጋራ በአል እንዲሆን ኮሚሽነሩ መመኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review