የሸገር ከተማን የመሬት ሀብት በአግባቡ ማስተዳደር የሚያስችል የልየታና ምዝገባ ስራ ተከናውኗል – የሸገር ከተማ አስተዳደር

You are currently viewing የሸገር ከተማን የመሬት ሀብት በአግባቡ ማስተዳደር የሚያስችል የልየታና ምዝገባ ስራ ተከናውኗል – የሸገር ከተማ አስተዳደር

AMN- ጥር 20/2017 ዓ.ም

የሸገር ከተማን የመሬት ሀብት በአግባቡ ለማስተዳደር፣ ለማልማትና ለታለመለት ዓላማ ለማዋል የከተማዋ የመሬት ልየታና ምዝገባ ስራ መከናወኑን አስተዳደሩ አስታውቋል።

በከተማዋ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማዘመንና ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

የሸገር ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ መኮንን አምቤ እንደገለጹት፤ በከተማዋ የደህንነት ካሜራዎች ተከላ፣ የእለት ተእለት የህዝብ አገልግሎቶች የሚበዙበት ተቋማትን በመለየት የአንድ ማዕከል አገልግሎት የማስፋፋትና የማጠናከር ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሸገር ከተማ ካላት 160ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ የ147ሺህ ሄክታሩን የመለየትና የመመዝገብ ስራ መጠናቀቁን ገልጸዋል ፡፡

ይሄ አሰራር አስተዳደሩን በሀገራችን የመጀመሪያ እንደሚያደርገውም አመልክተዋል ፡ በተለይም በየክፍለ ከተሞቹ ያሉ መሬቶች ለምን አገልግሎቶች እንደሚውሉ ተለይተዋልም ብለዋል።

የመሬት ልየታና ምዝገባው የከተማዋን መሬት ለተፈለገው ዓላማ ብቻ ማዋል እንዲቻል፣ በዘርፉ የነበረውን ሌብነት፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና የመሬት ምዝበራን ማስቀረት የሚያስችል ወሳኝ ተግባር መሆኑንም ተናግረዋል።

በተጨማሪም የሸገር ከተማን ስማርት ከተማ በማድረግ ለኑሮ አመቺና የኢንቨስትመንት ተመራጭነቷን ይበልጥ ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም ከተማዋን ከመሰረቱ ለመለወጥና ለቀጣይ ዘመናዊ እድገቷ መሰረት መጣል የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review