AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በሁሉም ክልሎች ለገነባቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 13 ሺ የተለያዪ የመርጃ መፅሀፍትን፣ 500 ታብሌቶችን እና 2 ሺህ 500 የሴቶች ንፅህና መጠበቂያዎችን አስረከበ፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የትምህርት ጥራትን እና ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት በርካታ ድጋፎችን በየክልሉ ለገነባቸው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያደርጋል፡፡

ለሴት ተማሪዎች ከተሰጠው የስነ ተዋልዶ እሽግ ውስጥ 2 ሺህ 500 የስነ ተዋልዶ ግንዛቤ ማስጨበጫ መፅሀፍት እንደተካተቱበት ከጽሕፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም ታብሌቶቹ መርጃ መፅሀፍት እንደተጫነባቸውም ነው የተገለጸው፡፡
የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ከዚህ ቀደም ለተማሪዎች ዪኒፎርም፣ አልባሳት፣ መማሪያ ደብተሮች፣ ኮምዩተሮች እና ሌሎች ቁሳቁሶችን በድጋፍ ሲሰጥ መቆየቱም ተመላክቷል፡፡