የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ለአካል ጉዳተኞችና የኦቲዝም ታማሚዎች የዊልቸር ድጋፍ አደረገ

You are currently viewing የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ለአካል ጉዳተኞችና የኦቲዝም ታማሚዎች የዊልቸር ድጋፍ አደረገ

AMN ግንቦት 20/2017

የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት ከቻይና የገጠር ልማት ፋውንዴሽን ጋር በጋራ በመሆን ያስመጣቸውን ዊልቼሮች በልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ለሆኑ አካል ጉዳተኞችና የኦቲዝም ታማሚ ህጻናት ድጋፍ አድርጓል።

ጽ/ቤቱ 46 ዊልቼሮችንና የስፖርት ቁሳቁስ ነው ድጋፍ ያደረገው።

የተደረገላቸው ድጋፍ ወገናዊነትን ያሳየና ለቤተሰብ እፎይታን የሠጠ መሆኑን የገለጹት ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤትን አመስግነዋል።

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review