AMN- ታህሣሥ 21/2017 ዓ.ም
የአሜሪካ 39ኛው ፕሬዝዳንት የነበሩት ጂሚ ካርተር በ100 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት በሞት ተለይተዋል።
የ2022 የሰላም ኖቤል ተሸላሚው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር በጆርጂያ ግዛት በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በወዳጅ ዘመዶቻቸው ተከበው በሰላም ማረፋቸውን “የካርተር ማእከል” በመግለጫው አስታውቋል።
የቀድሞው ፕሬዚዳንትን ህልፈት ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ፣ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንዲሁም የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
ጂሚ ካርተር ያቋቋሙት “የካርተር ማዕከል” የተሰኘው የእርዳታ ድርጅት ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ከ80 በላይ አገራት ላይ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው።