የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) መናኻሪያውን ጎብኝተዋል።
በ3 ነጥብ 9 ሄክታር መሬት ላይ አጠቃላይ ይዞታው ያረፈው መናኻሪያው በ1 ሰዓት ብቻ 120 አውቶብሶችን ማስተናገድ የሚችል ሲሆን፣ 7ሺ 200 ተሳፋሪዎችንም በሰዓት ማስተናገድ እንደሚችል የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ደንጌ ቦሩ ተናግረዋል።
መናኸሪያው 4ሺ800 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሁለገብ ህንጻ ያለው ሲሆን 13 የትኬት መቁረጫዎች፣ ካፍቴሪያዎች፣ ሱቆች፣ የስብሰባ አዳራሾች፣ የመመገቢያ ስፍራዎች ከ8ሺ ካሬ ሜትር በላይ የአረንጓዴ ስፍራ ከ1ሺ 130 በላይ ማረፊያ ወንበሮችን አካቷል።
የህዝብ ትራንስፖርት ስርዓቱን ለማዘመን እየተከናወነ ባለው ተግባር ተሳፋሪዎች በጸሀይና በዝናብ ሳይንገላቱ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል መናኻሪያዎችን ለማዘመን ለሚሰራው ስራ የአቃቂ መኽሪያ ሞዴል እንደሆነና የኤሌክትሮኒክስ የትኬት መቁረጫ ስርዓትንም እንደሚያካትት አቶ ደንጌ ገልጸዋል።
በቀጣይም የመርካቶ የሀገር አቋራጭ መናኻሪያን ጨምሮ ሌሎች መናኸሪያዎችንም የማዘመን ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል።
በሰብስቤ ባዩ