AMN- ጥር 12/2017 ዓ.ም
የቃና ዘገሊላ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሀገሪቱ በዛሬው ዕለት እየተከበረ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ከተማም በዓሉ በከተማዋ በተለያዩ ስፍራዎች እየተከበረ ይገኛል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ታቦቱ ካረፈበት ስፍራ ወደ ነበረበት ቤተክርስቲያን ለመመለስ እየተንቀሳቀሰ ነው።
ምእመኑም ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ ታቦተ ሕጉን እየሸኘ ይገኛል።
በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃና ዘገሊላ በሚባል አውራጃ ሰርግ ቤት ተገኝቶ ውኃውን ወደ ወይን የለወጠበት ቀን የሚታሰብበት መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ያስረዳል።