የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተጀመረ

You are currently viewing የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተጀመረ

AMN – ሚያዚያ 4/2017

የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ ተጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፥ በዘጠኝ ወራቱ በተለያዩ ዘርፎች የተከናወኑ ስራዎች እንደሚገመገሙ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

በግምገማው የሚቀጥሉትን ሶስት ወራት የስራ እቅድ ለማጠናከር የሚረዱ ውይይቶች እንደሚካሄዱ ጠቁመዋል።

እስከ አሁን ያሳካነው የሥራ ውጤት ሰፊ ቢሆንም ስኬታችን ሳያዘናጋን ለበለጠ ከፍታ የሚያነሳሳን ሊሆን ይገባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review