የባህር ዳር ዓለምአቀፍ ስታዲየም ግንባታ በአስደናቂ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing የባህር ዳር ዓለምአቀፍ ስታዲየም ግንባታ በአስደናቂ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ ይገኛል- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም

ስታዲየሙ ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ ባደረጉት ምልከታ ከነበረው ገፅታ በእጅጉ ተለውጦ ማየት መቻላቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፣ ምድረ ግቢው የተሻለ አምሮ የተመልካች ወንበሮች ገጠማ እየተፋጠነ፣ ሳሩ ተተክሎ እና ሌሎች የውስጥ ስራዎችን እየተሰሩ መመልከታቸውንም አንስተዋል።

የስታዲየሙ ግንባታ በሁሉም መሠረተ ልማቶች የካፍ እና ፊፋን ዓለም አቀፍ ደረጃ ጠብቆ በመጨረሻው የግንባታ ምዕራፍ ላይ ደርሷል ሲሉም አክለዋል።

ግዙፉ የባህር ዳር ስታዲየም ሀገራችን አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን እንድታስተናግድ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም አመላክተዋል።

በተጨማሪም ለባህር ዳር ከተማ ተጨማሪ ውበት፣ የገቢ ምንጭ እና ለስፖርት ዘርፉ መነቃቃት የሚኖረው አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በዚህ ዓመት መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር በጉብኝታቸው ወቅት መመልከት መቻላቸውንም ነው የገለጹት።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review