የባሎንዶርና ዓለም ዋንጫ የቀድሞ አሸናፊ ፋቢዮ ካናቫሮ ከዳይናሞ ዛግሬቭ አሰልጣኝነት ተሰናበተ

You are currently viewing የባሎንዶርና ዓለም ዋንጫ የቀድሞ አሸናፊ ፋቢዮ ካናቫሮ ከዳይናሞ ዛግሬቭ አሰልጣኝነት ተሰናበተ

AMN – ሚያዝያ 01/2017

የክሮሺያ ሊግ አሸናፊውን ዳይናሞዛግሬቭን ከሶስት ወራት በፊት የተረከበው ካናቫሮ ዛሬ ከኃላፊነት መነሳቱን ክለቡ አሳውቋል፡፡

ካናቫሮ በሁሉም ውድድሮች ክለቡን በ14 ጨዋታዎች በዋና አሰልጣኝነት መርቷል፡፡

በክሮሺያ ሊግ ብቻ አስር ጨዋታዎችን አድርጎ አምስት አሸንፎ፣ ሁለት አቻ ተለያይቶና ሶስት ተሸንፎ በደረጃ ሰንጠረዡ ሶስተኛ ላይ በመቀመጡ ነው ለስንብት የተዳረገው፡፡

የጣሊያን ብሄራዊ ቡድን የቀድሞ አምበልና ባሎንዶር አሸናፊው ፋቢዮ ካናቫሮ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ኤሲ ሚላንን 2ለ1 ያሸነፈበት ተጠቃሽ ስኬቱ ነው፡፡

ሳንድሮ ፔርኮቪች ፋቢዮ ካናቫሮን በመተካት የክለቡ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆነው እንዲሰሩ ኃላፊነት እንደተሰጣቸው ያሁ ስፖርትና ዋሽንግተን ፖስት ዘግበዋል፡፡

የ51 ዓመቱ ፋቢዮ ካናቫሮ ዳይናሞዛግሬቭን ከመረከቡ በፊት የዩዲኔዜና የቻይና ብሄራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት መምራቱ የሚታወስ ነው፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review