የባቱ – አርሲነገሌ የፍጥነት መንገድ ግንባታ 84 ነጥብ 50 በመቶ መድረሱ ተገለጸ

You are currently viewing የባቱ – አርሲነገሌ የፍጥነት መንገድ ግንባታ 84 ነጥብ 50 በመቶ መድረሱ ተገለጸ

AMN – መጋቢት 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል የሆነው የሞጆ-ሐዋሳ ኮንትራት 3 ፡ ባቱ – አርሲነገሌ የፍጥነት መንገድ ግንባታ 84 ነጥብ 50 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የዚህ ፕሮጀክት ግንባታ ሙሉ በሙሉ ከከተማ ውጪ የሚያልፍ ሲሆን ከከተማዎች ጋር የሚያስተሳስሩ አገናኝ መንገዶች ይሰሩለታል፡፡

የፍጥነት መንገዱ በ90 ሜትር የመንገድ ወሰን ውስጥ የሚገኝ ሆኖ ያለው አጠቃላይ የጎን ስፋት 31.6 ሜትር ሲሆን የአገናኝ መንገዶቹ ደግሞ በገጠር 10 ሜትር እና በከተማ ደግሞ 22.5 ሜትር ስፋት አላቸው፡፡

መንገዱን ለመገንባት የሚውለው 4.689 (አራት ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ) የተሸፈነው በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡

የአዲስ አበባ – ሞጆ – ሞያሌ – ላሙ – ሞምባሳ ትራንስ ኢንተርናሽናል ሀይዌይ አንድ አካል የሆነው ይኸው የመንገድ ኮሪደር -የባቱ ከተማ ፣ የአዳሚ ቱሉ እና አርሲ ነገሌ ወረዳዎች ብሎም ከ17 በላይ ቀበሌዎችን የሚያስተሳስር ነው::

በተጨማሪም በመስመሩ ላይ የሚገኙትን የእርሻና የኢንዱስትሪ እንዲሁም የቱሪስት መስህብ የሆኑ ቦታዎችን ለማገናኘት ያስችላል፡፡

ከዚህም ባሻገር የሞጆ-ሐዋሳ መንገድ 10,000 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የታላቁ የምስራቅ አፍሪካ ኮሪደር የደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ትራንስ አፍሪካን ሃይዌይ አካል በመሆኑ የአህጉራችንን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መንገድ መሆኑን ከኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review