የብላክበርን ሮቨርስ የቀድሞ አጥቂ ቤኒ ማካርቲ የኬንያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

You are currently viewing የብላክበርን ሮቨርስ የቀድሞ አጥቂ ቤኒ ማካርቲ የኬንያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ

AMN – የካቲት 24/2017 ዓ.ም

የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድን (ባፋና ባፋና) የቀድሞ አጥቂ ቤኒ ማካርቲ የኬኒያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን መሾሙን ሱፐር ስፖርት ዘግቧል።

የ47 ዓመቱ ቤኒ ማካርቲ የኬኒያ ብሔራዊ ቡድን በዚህ ወር በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከጋቦን እና ጋምቢያ ጋር ለሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ዝግጁ እንዲሆኑ እንደሚሰራ ይጠበቃል።

ማካርቲ በማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ቡድን ውስጥ የሆላንዳዊው አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ የቡድን አባል ሆኖ ማገልገሉ ይታወሳል፡፡

ማካርቲ ከማንቼስተር ዩናይትድ ከተሰናበተ ከወራት በኋላ ዛሬ የኬንያ ብሄራዊ ቡድንን ተረክቧል፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review