የብልጽግና ፓርቲ ከህዝቡ የተጣለበትን አደራ በትጋት ሊወጣ ይገባል:-የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች

You are currently viewing የብልጽግና ፓርቲ ከህዝቡ የተጣለበትን አደራ በትጋት ሊወጣ ይገባል:-የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች

AMN- የካቲት 15/2017 ዓ.ም

“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ በሁለተኛው የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ህዝባዊ ውይይት በአርባምንጭ ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የፓርቲውን የጉባኤ አቅጣጫ በተመለከተ የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል፡፡

ከቀረበው ሰነድ መነሻ የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪዎች፣ የብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ጊዜ ለህዝቡ የገባውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመድረኩ እንደገለጹት፣ በብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችን ለማሳካት በተደረጉ ሥራዎች ውጤት ተመዝግበዋል፡፡

ፓርቲው መላውን ህዝብ በማሳተፍ በሁለንተናዊ ልማት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ሥራዎችን ማከናወኑን ጠቅሰዋል።

የሃገሪቱን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት፣የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥና ዘላቂ ሰላምን መገንባት ረገድ መጠነ ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።

በገዢ ትርክት ግንባታና ብሔራዊ ጥቅምን በማረጋገጥ በኩልም አበረታች ለውጥ ተመዝግቧል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review