AMN – ጥር 22/2017 ዓ.ም
የብልፅግና ፓርቲ በመጀመሪያው ጉባኤው ላይ ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች መሬት ወርደው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እያደረጉ እንደሚገኙ ተገንዝበናልሲሉ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ።
“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ቃል ነገና ከነገ በስቲያ በአዲስ አበባ የሚደረገውን የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤን ለመሳተፉ ወደ አዲስ አበባ የመጡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ይነው።
የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በእስካሁኑ የአዲስ ኮንቬንሽን እና የኢግዚቢሽን ማዕከልን እንዲሁም በለሚ ኩራ የግብርና ምርቶች ማከፍፈያን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም መዲናዋን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግና በኑሮ ውድነት ላይ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።
በመዲናዋ እየተገነቡ ያሉ የልማት ስራዎች እና በቀጣይ የሚመለከቱትን መልካም ተሞክሮ ወደ አካባቢያቸው በመውሰድ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሰሩም አመራሮቹ ተናግረዋል።
ለብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ወደ መዲናዋ የመጡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በፓርቲው አመራር ሰጪነት እየተከናወኑ ያሉ ሌሎች የልማት ስራዎችንም እንደሚጎበኙ ይጠበቃል።
በራሄል አበበ