AMN – የካቲት 28/2017 ዓ.ም
ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ዛሬም ቀጥሏል፡፡
በመድረኩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የዘርፍ አመራሮች፣ የክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊዎች እና የክልል የአደረጃጀት እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመርሀ ግብሩ መሰረትም የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ በየደረጃው የተደረጉ ውይይቶች አፈጻጸም በተመለከተ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
በተያያዘም በፓርቲና በመንግሥት ቅንጅት የሚሰሩ የንቅናቄ ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ የሚደረግ ሲሆን፣ በስራ እድል ፈጠራ፣ ከኑሮ ውድነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት የሚከናወኑ ስራዎች እና ከተረጂነት ለመላቀቅ እየተሰሩ ያሉ ተግባራት ላይ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ከብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡