
AMN – ግንቦት 1/2017 ዓ.ም
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከአመራሩ እና ከሠራተኛው የሰበሰበውን 5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል አስረክቧል፡፡
በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች የተመራ የልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት የመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን በመዘዋወር ጉብኝት ካደረገ በኋላ፤ ከአመራሮችና ሠራተኞች የተሰበሰበውን የ5 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማዕከሉ መሥራች አቶ ቢኒያም በለጠ አስረክቧል።

የአገልግሎቱ ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከጉብኝቱ በኋላ እንደገለጹት፤ የመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነትን ወስዶ የሰብዓዊ ተግባር የሚፈጽም ባለውለታ ድርጅት መሆኑን ጠቁመዋል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በበጎ ተግባሩ እንዲሳተፍም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ የሚደረግላቸው አረጋውያን ለተደረገው እገዛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡