የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

AMN – የካቲት 22/2017 ዓ.ም

የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጥሪ አቀረቡ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ ፎረም በብራዚል መዲና ብራዚሊያ ተካሄዷል። በፎረሙ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ የብራዚል ኩባንያዎች፣ የንግድ ምክር ቤቶች እና የኢንዱስትሪ ፌዴሬሽኖች ተገኝተዋል።

ኩባንያዎቹ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን እና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው።

አምባሳደር ምስጋኑ በፎረሙ ላይ ኢትዮጵያ በግብርና ማቀነባበሪያ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ማዕድን ፣ቱሪዝም እንዲሁም በኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽንስ ቴክኖሎጂ (አይ ሲቲ) ዘርፎች ትኩረት በሰጠቻቸው ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርገዋል።

በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለው ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ሪፎርም በኢትዮጵያን ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ መፍጠሩን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ያላት መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ፣ ሳቢ የኢንቨስትመንት ፓኬጆች፣ ምቹ ፖሊሲዎች፣ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች የገበያ ተደራሽነቱን ይበልጥ እንዳሰፋው አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ እንዲሁም በአዲስ አበባ እና ሳኦ ፖሊ ከተሞች መካከል ያለው ዕለታዊ በረራ የብራዚል ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ እንዲሰማሩ ምቹ ዕድል የፈጠረ ነው ብለዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው የብራዚል ኩባንያዎች የኢትዮጵያን አዋጪ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።

በፎረሙ ላይ የተሳተፉ የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነወ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review