የቬትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ፋም ሚን ቺን በቤተ መንግሥታቸው ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ የአቀባበል ስነ-ስርዓት አድርገውላቸዋል።

You are currently viewing የቬትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ፋም ሚን ቺን በቤተ መንግሥታቸው ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይፋዊ የአቀባበል ስነ-ስርዓት አድርገውላቸዋል።

ከአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ በኋላ ሁለቱ መሪዎችና የልኡካን ቡድኖቻቸው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፥ በሁለቱ ሀገራት የተካሄዱ ማሻሻያዎችን እንዲሁም ለትብበር የሚሆኑ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተለይም የልምድ ልውውጥንና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

መሪዎቹ የትብብር ሰነዶችን የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይም የተገኙ ሲሆን፥ በንግድ እና በትምህርት ትብብር ላይ የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈርመዋል። በተጨማሪም በአዲስ አበባ እና በሃኖይ መካከል በኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀጥታ በረራ መንገድ የሚያመቻች የሲቪል አቪዬሽን ስምምነት ተደርጓል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የቬትናም ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተመሰረተ ከሃምሳ አመታት በኋላ የመንግስት መሪ ያደረጉት የመጀመሪያ ይፋዊ የኦፊሴላዊ ጉብኝት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በመረጃው አመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review