የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

You are currently viewing የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ

AMN – የካቲት 9/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን ከተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የዓለም አቀፍ አጋርነት እና የውጭ ግንኙነት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል ፋቱ ሀይዳር ጋር ተወያይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ ለምክትል ዳይሬክተር ጄኔራሏ በብሔራዊ የኢንዱስትሪ ልማት እየተተገበሩ በሚገኙ ፕሮጀክቶች ማለት በልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ፣በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በግብርና እና ምግብ ማቀነባበሪያ ዙሪያ ገለጻ በማድረግ የድርጅታቸው ድጋፍ አስፈላጊነት ገልጸዋል።

በውይይታቸው ኢትዮጵያ እና የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በቴክኒክ ድጋፍ፣በአቅም ግንባታ፣ በልምድ ልውውጥ እና በቴክኖሎጂ ልውውጥ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ምክትል ዳይሬክተር ጄኔራል ፋቱ ሀይዳር በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከወራት በፊት የተካሄደውን ከረሃብ ነጻ ዓለም ኮንፈረንስ በተሳካ መንገድ በማስተናገዷ አመስግነው ፤የተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review