የተርሚናል አገልግሎት አሰራር እና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ ዘርፉን በማዘመን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን እንደሚያሰፍን ተገለጸ

You are currently viewing የተርሚናል አገልግሎት አሰራር እና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ ዘርፉን በማዘመን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን እንደሚያሰፍን ተገለጸ

AMN – መጋቢት 5/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተርሚናል አገልግሎት አሰራር እና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ ዘርፉን በማዘመን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን እንደሚያሰፍን ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተርሚናል አገልግሎት አሰራር እና ቁጥጥር ረቂቅ ደንብ እና የማስፈጸሚያ ዕቅድ ላይ የአመራር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በውይይቱ ላይ የቀረበው ረቂቅ ደንብ ስርዓት እንዲከበር፣ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሳለጥ የላቀ አበርክቶ ከመኖሩም ባሻገር፣ የስራ እድል የሚፈጥር እና ወደ ኢንተርፕራይዝም የሚያሸጋግር መሆኑም ተገልጿል።

ረቂቅ ደንቡ በዘርፉ የሚነሱ ችግሮችን የሚቀርፍ እና ጥያቄዎችን የሚመልስ እንዲሁም ህገ ወጥ አሰራሮችን የሚቀርፍ እንደሆነም ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ፣ በመዲናዋ የተከናወኑ ጠንካራ የህግ ማስከበር ስራዎች አስተማማኝ ሰላም አስገኝተዋል፣ እነዚህን ውጤቶች ማጽናት ያስፈልጋል ብለዋል።

አዲሱ ረቂቅ ደንብ በዘርፉ ያሉ ማህበራት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እና የነዋሪውን የአገልግሎት ፍላጎት ለማሟላት አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል።

የህዝብን እንግልት መቀነስ እና ህግ እና ስርዓት እንዲከበር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ደንቡ አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል።

በደንቡ መሰረት ተራ አስከባሪዎች ተርሚናል ኢንተርፕራይዝ አገልግሎት በሚል ስያሜ አገልግሎቱን የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል።

የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ በበኩላቸው፣ የደንቡ አላማ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ማሳለጥ እና የትራንስፖርት ደህንነትን ማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የአደረጃጀት ችግሮችን ከመፍታት እና ዘርፉን ከማዘመን አኳያ የላቀ አበርክቶ አለው ብለዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review