የተሳሳቱ መረጃዎችን መታገል ሃገር ወዳድ ከሆነው የሚዲያ ባለሙያ እንደሚጠበቅ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ተናግረዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈፃሚው በሃገር እና በከተማ ደረጃ ለተመዘገቡ ውጤቶች የሚዲያ ባለሙያው አስተዋፅኦ የላቀ መሆኑን በማውሳትይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የሚዲያ ባለሙያው የሙያ ሥነ-ምግባርን የጠበቁ ተዓማኒ መረጃዎችን ለህዝቡ ተደራሽ ማድረግ አለበት ያሉት አቶ ካሳሁን ጎንፋ ፤ ከጋዜጠኞች ከወገንተኝነት የፀዳ እንዲሁም ሙያ እና ህዝብን መሰረት ያደረገ ዘገባ እንደሚጠበቅ አጽዕኖት ሰጥተዋል፡፡
“የተደራጀ ኮሙኒኬሽን እና ሚዲያ የሃገራዊ መግባባት ካስማ ፤ የትውልድ ግንባታ መሰረት ነው” በሚል መሪ ቃል የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የሚዲያ ባለሙያዎችና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች የጋራ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ በከተማና በሃገር አቀፍ ደረጃ በልማት፣ በሠላም፣ በዲፕሎማሲ፣ በትምህርት፣ በመልካም አስተዳደር እና በሌሎችም ዘርፎች በተመዘገቡ በርካታ ዉጤቶች ዙሪያ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
በውይይቱ ላይ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሞገስ ባልቻ፣ የሚዲያው የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም አጠቃላይ የሚዲያ ባለሙያው ተሳትፈዋል።
በሊያት ካሳሁን