የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ጸደቀ

You are currently viewing የተሽከርካሪ ሰሌዳ ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ጸደቀ

AMN – ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የተሽከርካሪዎች የመለያ ቁጥር ሰሌዳ አይነቶችና ምልክቶች መወሰኛ እና የአገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ 1050/2017 ሆኖ ጸድቋል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አማካሪ ከድልማግስት ኢብራሂም፣ የተሽከርካሪ ሰሌዳ መቀየርን አስመልክቶ ለዘርፉ የስራ ሀላፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም የሰሌዳ ለውጡ ዋና ምክንያት ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ታሳቢ ያደረገ ሰሌዳ እንዲኖር ለማስቻል ነው ብለዋል።

መመሪያው በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፣ በተመዘገቡና ለምዝገባ በሚቀርቡ ተሽከርካሪዎች፣ በተሽከርካሪ አምራች /አስመጪ/ገጣጣሚ ድርጅቶች፣ በተሽከርካሪ መዝጋቢ አካላት እንዲሁም በኢትዮጵያ በሚገኙ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት እና በግለሰቦች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሸከርካሪ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

May be an image of 1 person, dais, newsroom and text

See insights and ads

Boost post

All reactions:

101101

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review