የተሽከርካሪ ደህንነት ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት እስከ ምሽት 3፡30 ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወሰነ

You are currently viewing የተሽከርካሪ ደህንነት ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት እስከ ምሽት 3፡30 ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወሰነ

AMN- ሚያዝያ 19/2017 ዓ.ም

የተሽከርካሪ ደህንነት ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት እስከ ምሽት 3፡30 ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 86/2016 ከተሰጠው ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት ውስጥ በዘርፋ ለተሰማሩ ተቋማት ውክልና ሰጥቶ ማሠራት እንደሚችል ተቀምጧል፡፡

በዚህ መሰረት መንግስታዊ ለሆኑ እና መንግስታዊ ያልሆነ የተሽከርካሪ ደህንነት ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት (ቦሎ ቤቶች) ውክልና ሰጥቶ ያሠራል፣ ይደግፋል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ይመዝናል፣ አስፈላጊውን ማስተካከያም ያደርጋል፡፡

ባለሥልጣኑ ከሪፎርም ማግስት ጠንካራ የሥራ ባህል ገንብቶ ያስገኝውን ውጤት፣ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት አሰራራቸው ላይ ማሻሻያ ማድረግ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ እንደሚያምን አመላክቷል።

በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች በኢኮኖሚው ላይ የፈጠሩትን መነቃቃት አጠናክሮ በማስቀጠል፣ የከተማዋን ተወዳዳሪነት እውን ለማድረግ ቀን ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ በምሽት የንግድ እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጡበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ደንብ ቁጥር 185/2017 በማውጣት ተግባራዊ እንዲሆን መደረጉን አስታውሷል፡፡

በዚህ መሰረት ሁሉም የተሽከርካሪ ደህንነት ቴክኒክ ምርመራ ተቋማት (ቦሎ ቤቶች) በቀኑ ክፍለ ጊዜ የሚሰጡት አገልግሎት እንደተጠበቀ ሆኖ ከሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ምሽቱ 3፡30 ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ ውሳኔ መተላለፉን የባለስልጣኑ መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review