• አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና እና ተገቢውን ፍትህ እንድታገኝ ከአፍሪካ ህብረት እና ከሁሉም አባል ሀገራት ጋር በጋራ እንሰራለን
• አፍሪካ የሚታይ ተስፋ ያላት አህጉር ናት
• የቅኝ ግዛት ዘመን ጠባሳ ዛሬም ድረስ አፍሪካን እና አፍሪካውያንን እየጎዳ ነው፣ አፍሪካ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ አባል አለመሆኗ በቂ ማሳያ ነው
• በአፍሪካ አንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ችግሮች መኖራቸው አሳሳቢ ነው፣ ችግሮችን በመሳሪያ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ በመመካከር እና በመነጋገር መፍታት ይገባል
• አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለደረሰባት ችግር ፍትህ ልታገኝ ይገባል
• አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ሁለት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚደረገው እንቅስቃሴ ይቀጥላል
• በተመድ እና በአፍሪካ ኅብረት መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል
• በሱዳን፣ በኮንጎ፣ በሶማሊያ በመካከለኛው ምሥራቅ እና በሌሎችም አገራት ግጭት እና ቀጠናዊ ውጥረት መቆም አለበት።
• ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔን በመስጠት በሱዳን፣ በኮንጎ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ያሉ ግጭቶች በፍጥነት አፍሪካዊ መፍትሔ ማግኘት አለባቸው
• አፍሪካ ለነፃነቷ ያደረገችውን ጥረት አደንቃለሁ፣በቀጣይም ኢ-ፍትሐዊነት ተወግዶ ወደ ትክክለኛ ዕድገቷ እንደምትሄድ እምነት አለኝ
በወርቅነህ አቢዩ
AMN-የካቲት 9/2017 ዓ.ም