የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ ያለመ የ 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ እንደሚካሄድ ተመላከተ

You are currently viewing የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ ያለመ የ 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ እንደሚካሄድ ተመላከተ

AMN – ግንቦት 26/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የቱሪስት መስህቦችን ለማስተዋወቅ ያለመ የ 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

መነሻዉን ከሴቶች አደባባይ አድርጎ እስከ ሸራተን አዲሱ አስፓልት በሚዘልቀዉ በዚህ ሩጫ ላይ በኮሪደር ልማት የተሰሩ መዝናኛዎችን፣ ፓርኮች እና ሙዚየሞችን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ማርኬቲንግ እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ፍሬህይወት ገብረመድን ገልፀዋል።

ከ1 ሺህ እስከ 1 ሺህ 5 መቶ የሚሆኑ ሰዎች እንደሚሳተፉበት በሚጠበቀው በዚህ ሩጫ ላይ፣ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለሚወጡ አሸናፊዎች እንደየ ደረጃቸዉ ከ30 እስከ 20 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸዉ የአፍላንድ የምሽት ሩጫ ጀነራል ማናጀር አርቲስት ኢሳያስ መለሰ ጠቁመዋል፡፡

“እኔም አሻራዬን ላኑር” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደዉ የምሽት ሩጫ ላይ የመዲናዋን የልማት ስራዎች እና የመስህብ መዳረሻዎች በስፋት ያሳያል ተብሏል።

ሩጫዉን የአዲስ አበባ ከተማ ባህል፣ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ከአፍላንድ የምሽት ሩጫ ጋር በጋራ ማዘጋጀቱን በጋዜጣዊ መግለጫዉ ላይ ተመላክቷል።

ሩጫዉ ግንቦት 30 ከምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል ተብሏል።

በትባረክ ኢሳያስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review