
AMN ጥር 9/2017 ዓ.ም
የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቲክ ቶክ እንዲሸጥ አሊያም አሜሪካ ውስጥ እንዳይሰራ የተዘጋጀውን ሕግ ደግፏል፡፡
ባይት ዳንስ በተባለው ካምፓኒ የሚተዳደረው ቲክ ቶክ አሜሪካ ውስጥ ከ170 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚዎች አሉት፡፡
ቲክ ቶክ ለአሜሪካ ገዥ የማይሸጥ ከሆነ መተግበሪያው በሀገሪቱ የሚኖረው የአገልግሎት የመጨረሻ ቀን የፊታችን እሑድ እንዲሆን ቀነ ገደብ መቀመጡ ይታወሳል፡፡
የካምፓኒው ባለቤት ዣንግ ይሚንግ ካለው የቻይና ዜግነት ጋር ተያይዞ ቲክ ቶክ የአሜሪካ መንግሥት የብሄራዊ ደህንነት ስጋት ነው በሚል ሲያሟግት መቆየቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ዛሬ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት እግዱ ተግባራዊ ሲሆን መተግበሪያውን አዳዲስ ተጠቃሚዎች ማውረድ እንደማይችሉ እና ነባር ተጠቃሚዎች ደግሞ ማዘመን እንደማችሉ ለማወቅ ተችሏል።