የታይታኒክ መርከብ ስጥመት እና “ታይታኒክ” ፊልም!

You are currently viewing የታይታኒክ መርከብ ስጥመት እና “ታይታኒክ” ፊልም!

AMN-ሚያዚያ 05/2017 ዓ.ም

ግዙፏ ታይታኒክ መርከብ የሰጠመችው እ.አ.አ በ1912 ኤፕሪል 14 ነበር።

ከዛሬ 113 ዓመታት በፊት ከበረዶ ግግር ጋር ተላትማ አትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ የሰጠመችው መርከቧ 269 ሜትር ርዝመት እና ከ47 ሚሊዮን ኪ.ግ በላይ ክብደት ነበራት።

መርከቧ በ7.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በ3 ዓመት ወስጥ ነበር የተገነባችው።

ታይታኒክ ከእንግሊዝ ተነስታ ወደ ኒውዮርክ ጉዞ ከጀመረች ከ4 ቀን በኋላ ነበር በዛሬዋ ዕለት እኩለ ሌሊት አካባቢ 30 ሜትር ቁመት ካለው የበረዶ ግግር ጋር የተጋጨችው።

በአደጋው ወቅት ከ2 ሺህ 200 በላይ ሰዎች መርከቧ ውስጥ እንደነበሩ ይነገራል። ከእነዚህ ውስጥ ከ1500 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በህይወት የተረፉት ደግሞ 706 ሰዎች ብቻ ናቸው።

ከውቅያኖስ በታች በ3 ሺህ 840 ሜትር ጥልቀት የሰጠመው የታይታኒክ መርከብ ፍርስራሽ የተገኝው አደጋው ከደረሰ ከ73 ዓመታት በኋላ ነበር።

ከዚህ ጭብጥ በመነሳት የተሰራው የጀምስ ካሜሮን “ታይታኒክ” ፊልም 200 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የወጣበት እና እጅግ ተወዳጅ የሆነም ነበር። ፊልሙ በ11 ዘርፎች አካዳሚ አዋርድን አሸንፏል።

የታይታኒክ ፊልም መሪ ተዋናዮች ኬት ዊንስሌት እና ሊዮናርዶ ዲ ካፔሪዮ በተውኔት ዘረፍ ኦስካር አለማሸነፋቸው ብዙዎችን ያስገርማል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review