የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

You are currently viewing የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

AMN – መጋቢት 15/2017

በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ንቅናቄ መድረክ በባህር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፤ በኢትዮጵያ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህም መንግስት ለመማር ማስተማር ሥራው ምቹ ሁኔታ በመፍጠር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ባለው ቁርጠኝነት መሆኑን ገልጸዋል።

ችግሮችን በመቋቋም እየተከናወነ ያለውን የዘርፉን ሥራ ለማሳካት ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አመልክተዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በበኩላቸው፥ወቅታዊ ችግርን በመፍታት ለትምህርት ሥራ ውጤታማነት በየደረጃው ያለ አመራር፣የትምህርት ማህበረሰቡና ወላጆች በትብብር መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር)፥የዛሬው መድረክ ዓላማም በነበረው ችግር ወደ ትምህርት ገበታ ያልተመለሱ ህጻናትን ለመመለስ በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ለማጠናከር መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ እና በብልጽግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች እየተሳተፉ መሆናቸዉን ኢዜዘ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review