
AMN- ህዳር 5/2017 ዓ.ም
37ኛው የአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ማህበር መደበኛ የምክር ቤት ስብስባ መካሄድ ጀምሯል።
ማኅበሩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና አስተዳደሩ ጋር በመሆን የመምህራን ጥቅም ለማስጠበቅ የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ጠቁመዋል።
ይህ ተግባር መምህራን በስራቸው ላይ ትኩረት አድርገው ጥራት ያለዉ ትምህርት ተደራሽ እንዲያደርጉና ብቁ ዜጋ እንዲያፈሩ ዓለማን ያደረገ ሲሆን፤ በ37 ኛው መደበኛ ጉባዔው ይህንኑ ትኩረት በማድረግ የተለያዩ ውሳኔዎች ይወስናል ተብሎ ይጠበቃልም ብለዋል።
አስተዳደሩ ከዚህ ቀደም መምህራን በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው የቤት ባለቤት የሚያደርጋቸውን ዕድል መፍጠሩ፣ የደመወዝ ማሻሻያ፣ የትራንስፖርት አገልግሎትና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን እንዲያገኙ እያደረገ ያለው ተግባር በመልካም የተነሳ ሲሆን፤ ይሄው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።
የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ መምህራን ለበርካታ ዘመናት እያደረጉ ያለውን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም በጉባኤው ጥሪ ቀርቧል።
በአንዋር አሕመድ