የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ላለው ፈጣን እድገት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) ገለጹ።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የ2017 በጀት አመት ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ሀገር አቀፍ የሴክተር ጉባኤ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) እንዲሁም የፌደራል እና የክልል የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ አመራሮች ተገኝተዋል።
ሚኒስትር አለሙ ስሜ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ላለው ፈጣን እድገት የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኢኮኖሚውን በጉልህ የሚደግፉ ሰፋፊ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው ለዚህም የዘርፉ አመራሮች ጉልህ ሚና መጫወታቸውን ተናግረዋል።
ዘርፉ መድረስ ከሚገባው ደረጃ እንዲሁም ከኢኮኖሚው ግስጋሴ አንጻር ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን ጠቁመው ለዚህም ፈጠራ፣ ትብብር እንዲሁም ለስራ መትጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በመድረኩ የክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የአፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ኢዜአ ዘግቧል፡፡