
AMN- ጥር 15/2017 ዓ.ም
የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ከብሉምበርግ ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች መርሐ-ግብር ጋር በመተባበር የመንገድ ደህንነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት አካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ እንደገለጹት በከተማዋ የመንገድ ደህንነትን ለማስጠበቅ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል።
ባለስልጣኑን ጨምሮ 15 ተቋማትን ያካተተ የመንገድ ደህንነት ምክር ቤት በማቋቋምም የትራፊክ አደጋዎችን መቀነስ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

የብሉምበርግ አለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች መርሃ-ግብር ዋና ዳይሬክተር ርብቃ ባቪንገር በበኩላቸው የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ የህብረተሰቡን ግንዛቤ የሚያሳድጉ ስራዎች በትኩረት መሰራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።
በመንገድ ትራፊክ ደህንነት ዙሪያ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አመርቂ መሆናቸውን ገልጸው የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ጠቁመዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

All reactions:
39You and 38 others