ትላንት በተከበረው የትንሳዔ በዓል እና በዋዜማው ምንም ዓይነት የኃይል እጥረት አለማጋጠሙን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል የሪል ታይም ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጉልላት እንግዳ ገለጹ፡፡
ለበዓሉ ለመጠባበቂያ ከተያዘው ኃይል ውጪ ከ4 ሺህ ስምንት መቶ ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ለማቅረብ ዝግጅት ቢደረግም በዋዜማው 4 ሺ 624 ሜጋ ዋት እንዲሁም በበዓሉ ዕለት 3 ሺ 856 ሜጋ ዋት ኃይል ከፍተኛ የኃይል ጭነት መመዝገቡን ገልፀዋል፡፡
የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ለሆኑት የዳታ ማይኒንግ ኩባንያዎች፣ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች እና ለኤክስፖርት የሚቀርበው ኃይል ሳይቋረጥ ዝግጁ ከተደረገው ኃይል ውስጥ በዋዜማው176 ሜጋ ዋት እንዲሁም በበዓሉ ዕለት 944 ሜጋ ዋት ትርፍ ኃይል እንደነበር አቶ ጉልላት ማስረዳታቸዉን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡