AMN_የካቲት 18/2017 ዓ.ም
በቻይና ዓለም አቀፍ ንግድ ማስፋፊያ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ቼን ቺናን የተመራ የቢዝነስ ልዑካን ቡድን የቦሌ፣ ለሚ እና ቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎብኝተዋል።
የልዑካን ቡድኑ በጉብኝታቸው በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቹ ስላሉ የመሰረተ ልማት፣ የባለሀብቶች ተሳትፎ እንዲሁም አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ዙሪያ በቦሌ ለሚ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ስራ አስኪጅ አቶ ትንሳኤ ይማም፣ በቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ስራ አስኪያጅ ቶሎሳ በዳዳ (ዶ/ር) እና በኮርፖሬሽኑ አንቨስትመንት ፕሮሞሽን እና ማርኬቲንግ መምሪያ ኃላፊ ሚኪያስ ታደሰ ገለፃ ተደርጎላቸዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ተወካዮች የምክር ቤት አባላት እንደመሆናቸው ባለሃብቶች ኮርፖሬሽኑ በሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ሀብት እና እውቀታቸውን ስራ ላይ እንዲያውሉ ለማድረግ የሚያስችል የማስተዋወቅ እና የማግባባት ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሙ ዞኖች እና ድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ገብተው ስራ ከጀመሩ ባለሃብቶች መካከል የቻይና ባለሃብቶች ከፍተኛውን ቁጥር እንደሚይዙም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመለክታል፡፡