የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙ ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙ ጥሪ ቀረበ

AMN-ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም

ፍትሐዊ እና እኩል ተጠቃሚነትን የሚያሰፍነውን የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ቃል አቀባዩ ከቻይና ግሎባል ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት በተፋሰሱ አባል ሀገራት መካከል የልማት ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።

አምባሳደር ነብያት ይህን ፍትሐዊ እና እኩል ተጠቃሚነትን የሚያሰፍነውን የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን ያልፈረሙ ሀገራት እንዲፈርሙ በዚሁ ወቅት ጥሪ አቅርበዋል።

ስምምነቱ ወደ ተግባር መግባቱ በናይል ወንዝ ተፋሰስ የውሃ ዲፕሎማሲ ጉዞ ታሪካዊ ስኬት መሆኑን መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review