የናይጄሪያው ኤፒሲ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አልሀጅ አሊቡካር ዳሎሪ በብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

You are currently viewing የናይጄሪያው ኤፒሲ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አልሀጅ አሊቡካር ዳሎሪ በብልጽግና ፓርቲ ጉባዔ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገቡ

AMN-ጥር 22/2017 ዓ.ም

ሊቀመንበሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ፣ የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ኢፋ ሙለታ (ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ ጉባዔ ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ “ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

በጉባዔው ከ15 ሀገራት የተውጣጡ የጎረቤት ሀገራት እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች 43 ከፍተኛ አመራሮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review