የንብረት ማስመለስ አዋጁ ያለአግባብ ሀብት የማካበት እሳቤን ለማስቀረት ያግዛል-የህግ ምሁር

You are currently viewing የንብረት ማስመለስ አዋጁ ያለአግባብ ሀብት የማካበት እሳቤን ለማስቀረት ያግዛል-የህግ ምሁር

AMN-ጥር 7/2017 ዓ.ም

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሰሞኑ የንብረት ማስመለስ አዋጅን ማጽደቁ ይታወሳል፡፡

ኤኤምኤን የንብረት ማስመለስ አዋጁ አስፈላጊነት፣ አተገበባር እና በሚጠበቁ ውጤቶች ዙሪያ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቱ የህግ ምሁር እና ጠበቃ ከሆኑት አቶ ዘመድኩን መካሻ ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡

የንብረት ማስመለስ አዋጁ ህጋዊነትን የሚያሰፍን እና በአቋራጭ የመክበር እሳቤን በማስቀረት ሰርቶ ማደግ እና ሀብት ማካበት እንደሚቻል የሚረዳ ትውልድን ለመቅረጽ እንደሚያስችል የህግ ምሁሩ አቶ ዘመድኩን ተናግረዋል፡፡

ለሚያካብትው ሀብትም ህጋዊ አሰራርን የሚከተል ትውልድን በመቅረጽ በኩል ትልቅ ትርጉም ያለው ስለመሆኑ ምሁሩ አብራርተዋል፡፡

በተጨማሪም አዋጁ ከዚህ ቀደም የነበሩ ህጎች ይስተዋልባችው የነበሩ ክፍተቶችን የሚሞላ እንዲሁም አለም አቀፍ ህጎች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ለማስቻል ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አዋጁ ተግባራዊ ሲሆን የመንግስትን የመፈፀም እና ወንጀልን የመከላከል ምጣኔ ያሳድጋልም ብለዋል፡፡

አዋጁ በህዝብ እና በሀገር ላይ ትልቅ ለውጥን የሚያመጣ እና በሀገር ኢኮኖሚ ላይም ሚናዉ የጎላ በመሆኑ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማዳበር አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review