የንብረት ማስመለስ አዋጅ ጤናማና ፍትሃዊ የፋይናንስ ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል – ፍትህ ሚኒስቴር

You are currently viewing የንብረት ማስመለስ አዋጅ ጤናማና ፍትሃዊ የፋይናንስ ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል – ፍትህ ሚኒስቴር

AMN – ጥር 22/2017 ዓ.ም

የንብረት ማስመለስ አዋጅ ኢኮኖሚያዊ ወንጀሎችን ከመከላከል ባለፈ ጤናማና ፍትሃዊ የፋይናንስ ስርዓት እንዲኖር ያስችላል ሲሉ የፍትህ ሚኒስትር ሀና አርዓያስላሴ ገለጹ።

ሚኒስትሯ የንብረት ማስመለስ አዋጅና ከአዋጁ ጋር ተያይዞ ባሉት ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም አዋጁ ሰዎች በወንጀል በሚገኝ ንብረቶች ሀብት ለማካበት የሚያደርጉትን ጥረት ያስቀራል፡፡

በህገወጥ መንገድ ንብረት የሚያፈሩ አካላት ከዚህ ቀደም በወንጀል የሚጠየቁበት ስርዓት ያለ ቢሆንም ንብረቱ ተመላሽ የሚሆንበት ስርዓት እንዳልነበር አንስተዋል፡፡

አዲሱ አዋጅ በህገወጥ መንገድ የተገኘ ንብረቱ ተመልሶ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል እንደሚያደርግም ገልጸዋል።

አዋጁ ኢኮኖሚያዊ ወንጀሎችን ከመከላከል ባለፈ ጤናማና ፍትሃዊ የፋይናንስ ስርዓት እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።

ምንጩ ያልታወቀ ንብረትን አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን አዋጁ ከመውጣቱ በፊት እስከ 10 ዓመት እንዲሁም 10 ሚሊዮን ብር እና ከዛ በላይ ያሉትንም ተጠያቂ እንደሚያደርግ አብራርተዋል።

አዋጁን ለማስፈጸም የአሰራር መመሪያ ለማዘጋጀት ሚኒስቴሩ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

አዋጁ ሰዎች ከወንጀል ድርጊት የሚያፈሩትን ሀብት እና ምንጩ ሳይታወቅ የሚያገኙትን ንብረት በመቆጣጠር እና ሲገኝም ለማህበረሰቡ ተመላሽ እንዲሆን በማድረግ ወንጀል አትራፊ ሥራ እንዳይሆን እንደሚያደርግ ተመላክቷል።

የንብረት ማስመለስ አዋጅ ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጽደቁ እንደሚታወስ ኢዜአ ዘግቧል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review