የአሜሪካ ባለስልጣናት በቀጣይ ዙር ለሚደረገው የንግድ ድርድር ከቻይና ባለስልጣናት ተወካዮች ጋር በለንደን ተገናኝተው ሊነጋገሩ ቀጠሮ መያዛቸው ተገለጸ።
ነባሮቹ የነጩ ቤተመንግስት ባለስልጣናት በመጪው ሰኞ ከቻይና ባለስልጣናት ተወካዮች ጋር በለንደን ተገኝተው ስለቀጣዩ የግድ ንግግር ሊወያዩ መሆኑን ፕሬዝዳንት ዶልድ ትራምፕ ይፋ አደረጉ።
የመገናኘቱ ጉዳይ የመጣው ባለፈው ሐሙስ በፕሬዚዳንት ትራምፕ እና በቻይናው አቻቸው ሺ-ጂምፒንግ መካከል በተደረገው አንድ ሰዓት ተኩል ከፈጀ የስልክ ንግግር በኋላ መሆኑ ተዘግቧል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከሺ-ጂምፒንግ ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት ውስብስብ እና ቀናነት የታየበት እንደነበር እና በዉጤቱም አሜሪካ ብዙ ዶላሮችን ልታተርፍ እንደምትችል እምነታቸው እንደሆነ አርብለት በኤርፎርስ ዋን ተገኝተው ለሪፖርተሮች ባደረጉበት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቁመዋል።
አክለውም በቀጣይ ሰኞ በለንደን የሚደረገው የንግድ ንግግር በጥሩ ሁኔታ መካሄድ እንዳለበት አቅጣጫ የሰጡት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ አሜሪካንን ወክለው ለንደን የሚሄዱት ደግሞ፤የሃብት አስተዳደሩ ስኮት ቤሴንት፣ የወጪ ገቢ ንግድ ጸሃፊው ሃዋርድ ሉትኒክ እና የንግድ ጸሃፊው ጀምስ ግሪር መሆናቸውን ከእስካይ ኒውስ የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
ሀገራቱ በታሪፍ እና በወሳኙ ቻይና ዋና አምራች ሆና በቆየችበት የተፈጥሮ ማዕድናት ኤክስፖርት ውዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወሳል።
የጊዚያዊ ስምምነቱ አሜሪካ ቻይና ላይ ጥላው የነበረውን የ145 በመቶ ታሪፍ ወደ 30 በመቶ ሊያወርደው እንደሚችል ተጠቁሟል።
በወርቅነው አቢዮ